ስለ ወልቃይት ጠገዴው ጀግና ሻለቃ ጌታቸው ይርጋ (አባ ጣለው) – ከማስታወሻ ማህደር

ጌታቸው ይርጋ ከአባታቸው ከቀኛዝማች ይርጋ ነጋሽ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ብርጭቆ አድማሱ በ1927 ዓ/ም በወልቃይት ዓዲ ረመጥ ከተማ ተወለዱ። አባታቸው ቀኛዝማች ይርጋ ነጋሽ የጐንደር ክፍለ ሃገር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩ ናቸው። (ስለ ቀኛዝማች ይርጋ ነጋሽ ታሪክ አንድመጽሐፍ መጻፍ ይቻላል)። ጀግናው ጌታቸው ይርጋ ከሰቲት ሁመራ ግንባር ቀደም ባለሃብት ገበሬዎች አንዱ ነበሩ።

ሻለቃ ጌታቸው ይርጋ (አባ ጣለው)

ጌታቸው ይርጋ የደርግ መንግሥት ለመጣል ከተነሱት የወልቃይት ጠገዴ ጀግኖች የመጀመሪያው ግምባር ቀደም ከነበሩት አንዱ ናቸው ።ለምሳሌብንጠቅስ እነ ልጅ አቡሃይ አብተው፣ አቶ አዲሱ መኰንን፣ ቄስ ሲሳይ፣ አቶ ተድላ ወልደማርያም ፣ አብደሩሁማን ስራጅ፣ ታፈረ ኃይሌ፣ ባሻማእዛ ወዘተ ደርግ ገስጥ የሚባለውን ጦሩን ወደ ወልቃይት ጠገዴ (ሰቲት ሁመራ) ሲልክ የሁመራ ሕዝብ እነ ጌታቸው ይርጋ ጨምሮ ወደ ሱዳንመሬት ገዳሪፍ እና ሌሎች የሱዳን ከተሞች ሲሰደዱ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ደርግ የትግራዩን ገዥ የነበሩት ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም፣ ደጃዝማችሣሕለይ ኃይለሚካኤል፣ ደጃዝማች ወልደሥላሴ ኃይለሚካኤል ወዘተ የመሳሰሉ ወደ ሱዳን ሲያባርራቸው፣ ከጐንደር ጄኔራል ነጋ ተገኝ በግዜውየጐንደር ጠቅላይ ገዥ የነበሩ፣ እነ ፊተውራሪ ተስፋዬ አስናቀ ወዘተ ደርግ ስላባረራቸው ሁሉም በስደት የሱዳን መሬት ከተገናኙ በኋላ አንድ ላይግንባር ፈጥረው ደርግን ለመፋለም አቀዱ። አዲሱ ታሪክ እዚህ ላይ ነው ሚጀምረው።

የወልቃይት ጠገዴ ጀግኖች እነ ጌታቸው ይርጋ፣ ልጅ አቡሃይ አብተው፣ ሌሎችም በጣም ብዙ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች ያሉበት፣ የሽዋውአማራ ጄኔራል ነጋ ተገኝ እና የትግራዩ ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም በመሆን “ኤድዩ ” የሚባል ድርጅት መሰረቱ። ድርጅቱ ሲመሰረት አመራሮችሁነው የተመረጡት እነ ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም ለጌታቸው ይርጋ “ሻለቃ “የሚል ሹመት ሰጧቸው።

ሻለቃ ጌታቸው ይርጋ የታወቁ አነጣጥሮ በመተኮስ ክር የሚበጥሱ ጀግና ነበሩ። በፈረስ ስማቸውም “አባ ጣለው ጌቴ ” ይባሉ ነበር። ሻለቃ ጌታቸው ይርጋ አንበሳ በመግደላቸው “አንበሳ ገዳይ “በመባልም ይታወቁ ነበር።

ከደርግ ጋር ሽዋረስ ባሻ ማእዛ፣ ፊታውራሪ ተገኘ ቢተው የፈረስ ስሙ “ቆስቁስ ” ወጣቱ ወልቃይቴ ንጉሴ ወልዴ ወዘተ በአብደራፊ ውጊያ እነጀግናው ታፈረ ሃይሌ የመሳሰሉ፣ ለሃገራቸው ለአመኑበት የአመራር ስርአት ሲሉ ቢሰውም የመጀመሪያው ኃይለኛና ወሳኝ ውጊያ ግን ከደርግ ጋርየተካሄደው እና ብዙ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የተሰዋበት የመተማ ጦርነት በሻለቃ ጌታቸው ይርጋ የሚመራው የኤድዮ ሰራዊትና በደርግ ሰራዊትመካከል የተካሄደው ነው። በዚህ ጦርነት ሁለቱም ተፋላሚዎች ብዙ ሠራዊት ቢያልቅም ኤድዮ በዚህ ጦርነት ድል አልቀናቸውም። የጀግና ስምታሪክ ነውና ለግዜው ስማቸው ያገኘነውን በመተማ ጦርነት ሲዋጉ የተሰውቱን ጀግኖች ስማቸው ስንጠቅስ ያልተጻፉትን ግን የምታውቋቸው ካላችሁ በውስጥ መስመር ብትተባበሩን እንላለን። ከዝርዝሩ ውስጥ አቶ ተድላ ወልደማርያም፣ አቶ ሙሉ መሐሪ፣ አቶ አምባቸው ፈረደ፣ አቶ ዘውዱ አልጣህ፣ አቶ አብደሩሁማን ስራጅ፣ አቶ አምባሁነኝ ኃ /ሚካኤል፣ አቶ አለባ ኬዴ፣ አቶ አስማማው አድማሴ፣ አቶ አስረስ አባተ፣ አቶገብረመስቀል ገ/ሥላሴ እና በጣም ብዙ ወገኖቻችን እዚሁ ውጊያ መስዋእት ሁነዋል ።

ከዛ በመቀጠልም በሁመራ እና በተለያዩ አካባቢዎች ብዙ ጦርነቶች ተካሂደዋል። ግዜው እየገፋ ሲመጣ ጄኔራል ነጋ ተገኝ፣ ሌሎች መሰልየትግሉ አጋር የነበሩ ኮሎኔል፣ ሻለቃ በሙሉ ድርጅቱን እየጣሉ ወደ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ አሜሪካ መሄድ ጀመሩ፣ ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩምምከአሁኑ ሕውሐት ከድሮ ስሙ ትህነግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ከነሱ ጋር በምስጢር እንደሚሰሩ ተነቃባቸው። ነገር ግን የኛ የወልቃይት ጠገዴሰው የትግሬን መሰሪነት ባለማወቁና ልዑልን ያከብራቸውና ያምናቸው ስለነበር ማንም እሳቸውን ትቶ ሊሄድ ፈቃደኛ አልነበረም። በዚህ ወቅት ሁሉን ነገር ተረድተው ልዑል መንገሻን ትተዋቸው በመተማ በኩል አድርገው ጐንደር የገቡት ጀግናው ልጅ አቡሃይ አብተው ናቸው። ልዑል ራስ መንገሻ በዚህ የትግል ወቅት ሲያምኑት አሳልፎ ያስበላቸው የወልቃይት ጠገዴ ጀግኖች በጣም ብዙ ናቸው። ሰውየው ታሪክ ይቅርየማይለው ክህደት በወልቃይት ጠገዴ አማሮች ላይ ፈጽሟል።

የተባለውም አልቀረምና ሻለቃ ጌታቸው ይርጋ በ1982 ዓ/ም ሱዳን እምራኩባ ከሚባል ቦታ ከመኖሪያ ቤታቸው ድረስ የሱዳን መከላከያ ጦርበመምጣት ለጥያቄ እንፈልግህ አለን በማለት ወሰዷቸው። እሳቸውን ብለው ተከትለው የሄዱት 13 ሰዎች ሳይቀር ሳይመለሱ ቀሩ አብረውአጠፏቸው። ጀግኖቻችን ሞቱ ተብሎ አልተለቀሰ አሉ ተብለው አልተፈቱ በከንቱ ዘመን ተቋጠረ ።ለዚህ የአረመኔ ስራ ተጠያቂው ግን ልዑል ራስመንገሻ ስዮም እና ልጃቸው ስዮም መንገሻ መሆናቸው ሁሉም ታሪኩን አውቃለሁ የሚል እየመሰከረበት ነው። ለግዜው ስማቸውን ያገኘነው፤ አቶ አስራደ በየነ ፣አቶ ሃጐስ ጌታሁን ፣አቶ መከታው አዛናው ፣አቶ እናሩ ገብረሕይወት ናቸው። የተቀሩትን ጀግኖች የምታውቁ ካላችሁ ታሪክጠፍቶ እንዳይቀር ስማቸውን በውስጥ መስመር ብታደርሱን ምስጋናችን ወደር የለውም።

ከሁሉም የሚገርመው ግን ወያኔ ወደ ሥልጣን ሲመጣ፣ የልዑል ዘመዶች በትግራይ ምኒሊክ ግቢ ሲገቡ እሳቸው ደግሞ በቦሌ አይሮፕላንማረፊያ አይናቸውን በጨው አጥበው አዲስ አበባ ገቡ። የወልቃይት ጠገዴ ጀግኖቻችን ግን ደማቸው ደመ ከልብ ሁነው ቀሩ፣ ታሪክ ይፍረደው። ሌላው ቢቀር እንኳን ጀግኖቻችን ለአገራቸው ለአላማቸውሲሉ የተሰው ስለሆነ የሰሩትን ጀብድ ታሪክ ነውና ተጽፎ ለልጅ ልጆቻቸው ሊቀመጥ ይገባ ነበር፣ የሌሎች ደርጅቶች መሪ የነበሩ ስለ ድርጅታቸውታሪክ ሲጽፉ “ኤድዮ” ግን እስካሁን የፃፈው ምንም ነገር የለም ።

አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ልዑል የወልቃይት የአማራ ብሔርተኝነት ከተነሳ በኋላ በአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ( VOA) ቀርበው “እኔ እስካስተዳደርኩበት ግዜ የትግራይ ደምበር ተከዜ ነው” ስላሉ እውነት ተናጋሪና ጥሩ ሰው አድርገው ሲስሏቸው አያለሁ፣ ነገር ግን ቆም ብለንብናስብ እኒህ ሰው ከነ ኮለኔል ደመቀ ወይም ከሌሎቹ እሥር ቤት ታጉረው የሚሰቃዩ ያሉ ወገኖቻችን ምን የተለየ አልተናገሩም እናም ልናመሰግናቸው አይገባም። እሳቸው ይህን ተናግረው በነጻነት አዲስ አበባ አሜሪካ ይንሸራሸራሉ ምሲኪኑ ወገናችን ግን በየእሥር ቤቱ በግርፋትይማቅቃል። ይሄንን እውነት ግን አስበነው አናውቅም። እኛ እውነት ስንናገር የሚጠብቀን የወልቃይት ኮሚቴዎች እጣ ፈንታ ነው። ደግሞስ እንደ ልዑል መንገሻ ከሕውሓት በላይ የወልቃይት ጠገዴን ሕዝብ የበደለ አለ እንዴ? ጀግኖች ወንድሞቻችና አባቶቻችን ያሳጣንና ወደትግራይ እንድንከለል ብዙ ነገር ያደረገ ታሪክ ነገ የሚያጋልጠው ሰው ነው። አሁን ለማስመሰል የተናገረውን ማመን የለብንም። እስኪ ይህንመግለጫ ሌላ ሰው ይስጥና የሚያጋጥመውን እንመልከት፣ ወገኔ ሆይ ያለፈው አልፏልና ከፊት ለሚጠብቀን ነገር ነቃ እንበል።

ወልቃይት ጠገዴ እልፍ ጀግኖች ያፈራች የአማራ ምድር ነች፣ ነገር ግን ጀግኖቻችን የታሪክ ድርሳናትን ስናገላብጥ የምናገኛቸው በጣም ውስኖች ናቸው። ይሄ ለምን ሆነ ብለን ስንጠየቅ መልስ አናገኝም። ዋልድባ ገዳም፣ጠገዴ እንዳማርያምና በተለያዩ አብያተ ክርስትያናት የነበሩት የታሪክ ድርሳናት እኛ ባለመንቃታችን ዛሬ ወያኔ የት እንዳጠፋቸው አይታወቅም። ይሄ ደግሞ የበለጠ ያሳምማል።

አንተ አዲስ ትውልድ ሆይ ብዙ ስራ ይጠብቅሃልና ራስህን አዘጋጅ!

ወልቃይት ጠገዴ አማራ ነው!

እኛም የአባቶቻችንን ጀግንነት የተላበስን ልጆች ነን!
minilikawi Bitwoded